ክፍለ ትምህርት ፪ : የቤተክስቲያን የውስጥ ክፍሎች
- ሶስቱ የቤተ-መቅደስ ክፍሌች እና ትርጉማቸው፡-ወደ ቤተ-መቅደስ ስንገባ በሶስቱም የቤተ-ማቅደስ አሰራር አይነቶች ዘንድ በውስጣቸው የምናገኛቸው ሦስት ክፍሎች አሉ ፡፡
እነሱም፡- 1) መቅደስ
2) ቅድስትና
3) ቅኔ ማህሌት ይባላሉ ፡፡
ሦስት የሆኑበት ምክንያት ፡-
1.በሦስቱ ዓለማተ መላዕክት (የመላዕክት ከተሞች)ምሳሌ፡- ኢዮር ፣ ራማ ፣ ኤረር በመባል ይታወቃሉ ፡፡
2.በሦስቱ ማዕረጋተ ክህነት ምሳሌ ፡- ድቁና ፣ ቅስና ፣ ኤዸስቆዾስ (ዻዻስ)
3.በሦስቱ ፆታ ምዕመናን ምሰሌ ፡- ካህናት ፣ ሴቶች ፣ ወንዶች
4.የሦስቱ ኆኅተ ገነት (የገነት በሮች ምሳሌ)
5.በታቦተ አዳም
6.በታቦተ ሙሴ እና በታቦተ መላዕክት አምሳል
7.ፅርሐ አርያም
8.በኢዮርእና በጠፈር አምሳል ፡፡
አገልግሎታቸው
1)ቅኔ ማህሌት፡-ስያሜው የግበረ የተወረሰ ነው ፡፡ መዝማራነ ፣ ደባተ ካህናት ስብተ እግዚአብሔር ማህሌትር እግዚአብሔር በመአልት በለሊት የሚያቀኙበት ነው ቅኔ የሚቀኙበት ቀሳውስት የሚያስተዛዝኑበት ክፍል ነው መዝሙር የሚዘምሩበት ክፍል ነው ፡፡
- በጥንት ዘመን ስርአተ ጥምቀት የሚፈፀምበት በዚህ ክፍል ነበር።
- በዚህ ክፍል በስመዕ (ሰሜን ምስራቅ) ንዑስ ማዕዘን በኩል ቀሳውስትና ዲያቆናት በመንፈቀ ሌሊት ሰአታት በነግህ ኪዳን ያደርሲበታል ፡፡
- በዚህ ክፍል ለጥምቀት ለቁርባን ያልበቁ በትምህርት ንስሀ የሚፈተኑ አዲስ አማኞች (ንዑስ ክርስቲያን) ዲያቆኑ “ፂኡ ንዑስ ክርስቲያን” ብሎ እስኪያውጅ ድረስ በእዚያ ይቆያሉ ከዚያም ቃጭል ተመቶ አዋጅ ሲታወጅ ይወጣሉ - ይህ ክፍል ወንዶች ምዕመናን ቆመው የሚያስቀድሱበት ቦታ ነው።
- በዚህ ክፍል ሌብ(ደቡብ ምስራቅ) ንዑስ ማዕዘን በኩል የሚገኘው ቦታ የሴቶች መቆሚያ ነው ።
- ይህ ክፍል ከውጭ ወደ ቤተ-መቅደስ ስንገባ የምናገኘው የመጀመሪያው ክፍል እንደመሆኑ ወደ ውስጥ የምንገባባቸው ሦስት በሮች በሏት የካህናት ፣የወንዶች ምዕመናን እና የሴቶች ምዕመናን መግቢያ ናቸው።
- በቤተክርስቲያን ስርአት ወነወዶችና ሴቶች አብረው ቆመው ስለማፀልዩ በመጋረጃ የከፈላሉ ።
- ክፍሉ በምስራቅ ፡-የካህናት፣ በሰሜን የወንዶች በደቡብ የሴቶች መግቢያ ነው ፡፡
2)ቅድስት፡-ትርጉሙ የተለየ ልዩ ማለት ሲሆን ይህ ክፍል በቤተክርስቲያን ማዕከላዊ ቦታ ነው የሚገኘው ፡፡
- ይህ ክፍል ካህናት በድርነት ጊዜ ምዕመናንን የሚያቆርቡበት ክፍል ነው።
- በስብከተ ወንጌል ሰአት መምህራን ቆመው የሚያስተምሩበት ክፍል ነው።
- በተክሊልና በቁርባን አንድ ለሚሆኑ ሙሽሮች ጸሎት የሚደረግበትና በካህናት እጅ የሚባረኩበት ክፍል ነው።
- በስቅለት እለት ስርአት ጸሌት የፈጸምበታል ።
- በዚህ ክፍል የሚቆሙት ፤በምዕራብ በኩል የሚቆሙት ናቸው፤ በሰሜን በኩል የሚቆሙት መነኮሳት እና ወንዶች ምዕመናን ናቸው ፤ በደቡብ በኩል የሚቆሙት ደናግል ፣የቀሳውስትና የዳቆናት ሚስቶች ናቸው በዚህ ክፍል ቆመው ላስቀደሱት ምዕመናን ስርአተ ቁርባን የፈጸማል በምስራቅ ፣ በምዕራብ ፣ በሰሜን ፣ በደቡብ አራት በሮች ይኖሩታል የማይቆርቡ ምዕመናን በዚህ ክፍል ቆመው ማስቀደስ የለባቸውም ፡፡
3)መቅደስ፡- ይህ ስፍራ ስልጣነ ክህነት ያላቸው በቻ ለቅዳሴና ለጸሌት እጣን የሚያደርሱበት ታቦተ ህጉ የሚኖርበት መስዋዕተ እግዚአብሔር ስጋ ወደሙ የሚሰዋበት ቦታ ነው
- መቅድስ የእመቤታችን ምሳሌ ነው።
- ከመቅደስ መስዋተ ኦሪት እንደሚገኝ (1ኛነነስት 8÷1-66)መስዋተ አዲሰ ከድንግል ማርያም ተገኝቷልና በብሉይ ከዳን ቅድስተ ቅዱሳን በሚል ስያሜ ከሚታወቀው ውስጠኛው ክፍል ጋር የሚነፃፀር ነው ።
- ይህ ክፍል የቃልኪዳን ታቦት ሌሎች ነዋየ ቅዱሳት በዚህ ክፍል ይገኛሉ።
- ብጹ ወቅዱስ ፓትሪያሊኩ ፣ ብጹሀን ሊቃነ ዻዻሳት የሚያስቀድሱት በዚህ ክፍል ነው።
- በምዕራብ፣ በሰሜን ፣ በደቡብ ሦስት በሮች ይኖሩታል እያንዳንዱ በር መንጦላይት (መጋረጃ)አለው።
- የጌታችን ስጋና ደሙ የሚፈተትበት በዚህ ክፍል ነው ፡፡
በቤተ-መቅደስ ዙሪያ የሚገኙ ነዋየ ቅዱሳት እና ምሳሌያዊ ትርጉማቸው
በቤተክርስቲያን የምናያቸው እያንዳንዳቸው ቅዱሳትና ነዋያት ራሱን የቻለ ምሳሌያዊ ትርጉም አለው በቤተክርስቲያን ዙሪያ ያሉ የሚተከሉ ምሰሶዎች የሚቆሙት ደረጃዎች የሚሰሩት ግድግዳዎች ና እጽዋቶች የሚያስተላልፉት መልእክት አላቸው ፡፡
በዚህም አንድ ክርስቲያን ወደ ቤተ-መቅደስ ሲገባ የሚመለከተው በእያንዳንዱ ነገር እግዚአብሔር በአንቀጸ ህሊና በነወፃ ልቦና መንፈሳዊና ሰማያዊ ሚስጥር እንዳያስበው ያደርገዋል ፡፡
1.ጉልላት፡-የቀራንዮ ምሳሌ ነው ፡፡ በቤተክርስቲያን አናት ላይ እንደ ተራራ ሆኖ የምናየው ጉልላት ጌታችን የሰው ልጅን ለማዳን የተሰቀለበት የቀራኒዋ ምሳሌ ነው ጉልላትና በላዩ የተሰቀለውን መስቀለ ስንመለከት ጌታችን ለድህነተ ዓለም በቀራንዮ (በጎለጎታ) መሰቀሉን እናስባለን ፡፡ ዩሐ19÷17 “ከዚህ በዋላ ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ “የራስ ቅል” ወደ ሚባልም ስፍራ መጣ ” ይህ ስፍራ (ዕብራይስጥ) ቋንቋ በጎለጎታ ይባላል ፡፡
2.በጣሪያው ዙሪያ የሚደረጉና የሚንሻሹ(ሻኩራዋች)፡- የቅዱሳን መላዕክት ምሳሌ ናቸው ፡፡ ሻኩዎች ሌሊትና ቀን እየተወዛወዙ ድምፅ እንደሚሰጡ ቅዱሳን መላዕክ በቤተክርስቲያን አዕድ ሌት እና ቀን ያሸበሽባሉ የዘምራሉ ፡፡(ዘፍ 28÷11-17)
3.የሰጎን እንቁላል፡-ቤተክርስቲያን አናት የሰጎን እንቁላል ይደረጋል ፡፡ ይህ እንቁላል ሚስጥራዊ ትርጉም አለው ሰጎን እንቁላልን እንዲፈለፈል የምታደርገው ታቅፋ ሳይሆን ወዲያ ወዲህ ስትል ትኩር ብላ በማየት ነው ሰጎን እንቁላሏን ያለማቋረጥ እንደምትመለከት እግዚአብሔርም ፍጥረቱን የማይረሳ በፀጋውና በረድኤቱ ከፍጥረቱ የማይለይ መሆኑን ለማጠየቅ የሰጎን እንቁላል በቤተክርስቲያን አናት ላይ ይሰቀላል እንቁላሉ በምዕመናን እና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ያስረዳል ፡፡ “ምክንያቱም እኔ ይህ ቤተ-መቅደስ መርጨዋለው ፤ለዘላለም የሚመለከተው ስፍራ ይሆን ዘንድ ቀድሼዋለው በልቤም ውስጥ አድርጌ ዘወትር እጠብቀዋለው”(2ኛመ 9÷16)
4.ሶስቱ በሮች ፡-ወደ ቤተ-መቅደስ የምንገባባቸው ሦስት በሮች በሰሜን እና ደቡብ እንዲሁም በምስራቅ የሚገኝ የገነት በሮች ምሳሌዎች ናቸው በገነት ሶስት በሮች ነበሮተረ በምስራቅ በር እግዚአብሔር በሰሜን በር አዳም በደቡብ በር ሄዋን የገቡበት ነበር ፡፡
ምሳሌዎች ፡- ሚስጥረ ሥላሴ(ቅድስት ስላሴ )፣ ሦስቱ ሰማያት (አለማተ መላዕክት ) በኢዮር፣በራማ፣በኤረር ምሳሌ ነው ፡፡
1.አእማድ ፡- ማለት ምሰሶ ማለት ነው ፡፡ ቤተ-መቅደስ ውስጣዊ ክፍል በኩል የሚተከሉ ናቸው ፡፡
2.በቅዱሳን መላእክት፡-መላዕክት በእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ ዙሪያበምስጋና፣ፀሎትን ለማሳረግ ፣እንዲሁም ለጥበቃ ሌትና ቀን ሳያርፉ እንዲቆሙ ሁሉ ምሰሶ ወይም አዕማድዎቹም ሌትና ቀን ተተክለው ይታያሉ ፡፡
3.በቅድሳን ሀዋርያት ፡- አባቶቻችን ቅዱሳን ሀዋሪያት ሌትና ቀን በአገልግሎት ፀንትው ቤተክርስቲያን እንዳያገለግሉ ለማሳየት ምሰሶዎቹም ፀንተው ይታያሉ ሀዋርያው ቅዱስ ዻውሎስ የሀዋሪያነት አባቶቻችን ምሰሶነት ፣ ዋነኝነት (ታላቅነት) ሊገለፅ “አእማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋው ዩሀንስም …፡፡”በማለት ያስቀምጣል ፡፡ ገላ 2÷7
በቤተክርስቲያን ዙሪያ የግድ መሰራት ያለባቸው ነገሮች
. ቤተልሄም፡- ስጋ ወደሙ በቤተ-መቅደስ በስተምስራቅ የመ፣ገኝ ቤት ነው ፡፡ ሌላኛው መሰዊያ የሚቀርብበት (መገበሪያ) የሚሰየምበት በቤተክርስቲያን ቅጥር ጊቢ የሚሰሩ ሁለተኛው ቤት አለ ይህ ቤት የግብር ቤት ይባላል የቤተክርስቲያን ነዋየ ቅድሳት የሚቀመጠበት ቤት እቃ ቤት ይባላል ስርአተ ጥምቀት የሚፈፀምበት የመጠመቂያ ቤት አለ በዚያም ሌላ በገጠሩ ባ አብያተ ክርስቲያን የሙታን በደን የሚያርፉበት እና ፀሎት ፍትሀት የሚፈፅሙበት ደጀሰላም ከቤተክርስቲያን ቅጥር ተያይዘው ይሰራሉ ፡፡
- በምዕመናን አቅም ሊሰሩ የሚገባቸው ቤቶች ፡-
- የሰበካ ጉባኤ ፅፈት ቤት
- የሰንበት ትምህርት ቤት
- የስብከተ ወንጌል አዳራሽ
- የእንግዳና የካህናት ማረፊያ ቤቶች
- የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት
- ቤተ-መጽሐፍት
- የነዋያተ ቅዱሳት ሱቆች መገንባት ይቻላል ፡፡
- ሰንበቴ ቤት ፡-ምዕመናን በሰንበት እለት ተሰብስበው የሰንበት ፅዋ እየጠጡ በካህናት አባቶች የሚሰጠውን ትምህርት የሚያዳምጡበት እርስ በርሳቸው የሚጠያየቁበት ቤት ነው ፡፡ ይህ ቤት አፅድ አርባ ክንድ ተጠግቶ የሰራል ፡፡
- ቤተ-ምርፋቅ ፡-ምራፋቅ ረፈቀ ከሚለው የግስ ግስ የተገኘ ሲሆን የሰደቃ ቤት ፣የምግብ ቤት (ቦታ)ደስ ማለት ነው ካህናት ከተልዕከ (ከቅዳሴ)ከማህሌት በኃላ አርፈው እህል ውሀ የሚቀምሱበት ቤት ነው ፡፡ በልማዳዊ አሰራር ይህ ቤት ደጀ ሰላም ይባላል ፡፡ ይሁንና ደጀ ሰላም በጥንት ጊዜ በቤተክርስቲያን መግቢያ በር ላይ ተያይዞ የሚሰራ የገነት ምሳሌ ነው ምዕመናን ፣ በቁርባንና ለክርስትና ያመጡትን እህል ውሀ አቅርበው ከአባቶች በረከትን የሚቀበሉበት ቤተ-ምርፋቅ ይባላል ፡፡
በቤተክርሰቲያን ውስጥ ሊሠሩ የማይገባቸው
1.መቃብር
2.ሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ (ከንዋየ ቅዱሣት ውጭ)